ጋና ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ሶስተኛ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ጋና አልጄሪያን በመለያ ምት በማሸነፍ የመጨረሻ አራት ውስጥ ገብታለች።

ማምሻውን በቤርካኔ ሙኒሲፓል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በመደበኛ 90 ደቂቃ ምንም ግብ ባለመቆጠሩ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።

በጭማሪ ሰዓቱም ሁለቱ ቡድኖች ግብ ባለማስቆጠራቸው ወደ መለያ ምት ማምራታቸው ግድ ሆኗል።

ጋና በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። በግማሽ ፍጻሜው ከአዘጋጇ ሞሮኮ ጋር ትገናኛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም