ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያገኘችውን የሜዳሊያ ብዛት ወደ ስድስት ከፍ አደረገች 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፦ በናይጄሪያ አቡካታ እየተካሄደ ያለው ሶስተኛው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

አመሻሹ ላይ ከ18 ዓመት በታች በ3000 ሜትር ሴቶች በተካሄደ የፍፃሜ ውድድር አትሌት ደስታ ታደለ የብር ሜዳሊያ ማግኘቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። 

አትሌት ብርነሽ ደሴ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።  

አትሌት ደስታ ታደለ ከ18 ዓመት በታች ትናንት በ1500 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ የሚታወስ ነው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘችውን የሜዳሊያ ብዛት ወደ ስድስት ከፍ አድርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም