ጣልያን ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች - ኢዜአ አማርኛ
ጣልያን ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2017(ኢዜአ)፦ በ14ኛው የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ጣልያን ኖርዌይን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
ማምሻውን በጄኔቭ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክርስያቲያና ጂሬሊ ሁለቱንም ግቦች አስቆጥራለች።
አዳ ሄገርበርግ ለኖርዌይ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ተጫዋቿ በጨዋታው ላይ የፍጹም ቅጣት ምት ስታለች።
ጣልያን በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን በመፍጠር ከተጋጣሚዋ የተሻለች ነበረች።
የጣልያን ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዋ የ35 ዓመቷ ክርስቲያና ጂሬሊ ያስቆጠረቻቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 61 ከፍ አድርጋለች።
ውጤቱን ተከትሎ ጣልያን ግማሽ ፍጻሜ የገባች የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች።
በግማሽ ፍጻሜው ከስዊድን እና እንግሊዝ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።