የመጅሊስ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል

 

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 9/2017(ኢዜአ)፦የመጅሊስ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የመጅሊስ ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ገለጸ።

የምርጫ አስፈፃሚ ቦርዱ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን እና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት በኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ አብዱልአዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የዘንድሮው የመጅሊስ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

ቀሪ ስራዎች እስከ ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚጠናቀቁ ይሆናል ብለዋል።

ቀሪ ውስን ስራዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጅሊስ ምርጫ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም መካሄድ ይጀምራል ብለዋል።

የኡለማ የምርጫ ዘርፍ ነሐሴ 9 ቀን 2017 እንደሚካሄድም አመላክተዋል።

ነሃሴ 11 ቀን ጠዋት ደግሞ የምሁራንና የወጣቶች እንዲሁም ከሰዓት የሴቶችና የሰራተኛ ክፍሉ ምርጫ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

ነሃሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የስራ አስፈጻሚ ፕሬዝዳንትና ወሳኝ ሃላፊዎች ተመርጠው ቀጥሎ ባሉት ሁለት ቀናት ተመራጭ አመራር ከነባሩ አመራር የሃላፊነት ርክክብ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም