ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማዋ የምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማዋ የምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ የምክር ቤት አባላት በእንጦጦ ተራራ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል።
ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ በሁሉም አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።