ታንዛንያ እና ደቡብ አፍሪካ ነጥብ ተጋርተዋል

 አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት መርሃ ግብር ታንዛንያ እና ደቡብ አፍሪካ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ትናንት ማምሻውን በሆነር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አጥቂዋ ኦፓ ክሌመንት በ24ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ግብ ታንዛንያ መሪ ሆናለች።

የተከላካይ መስመር ተሰላፊዋ ባምባናኒ ምባኔ በ70ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ጎል ደቡብ አፍሪካን አቻ አድርጓል።

የታንዛንያዋ ኤልሳቤት ጆን ቼንጌ በ84ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ሜዳ ተሰናብታለች።

የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ደቡብ አፍሪካ በአራት ነጥብ የምድቡን መሪነት ከማሊ ተረክባለች።

ታንዛንያ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ጋና እና ማሊ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ደቡብ አፍሪካ ከማሊ፣ ጋና ከታንዛንያ የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም