ጋና እና ማሊ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ጋና እና ማሊ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በቤርካኔ ሙኒሲፓል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአማካይ መስመር ተሰላፊዋ አሊስ ኩሲ በስድስተኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ ጋናን መሪ መሆን ችላ ነበር።

ከእረፍት መልስ አጥቂዋ አይሳታ ትራኦሬ በ52ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ግብ ማሊን አቻ አድርጋለች።

በጨዋታው ብልጫ ወስዳ የተጫወተችው ጋና ያገኘቻቸውን ግልጽ የግብ እድሎች አልተጠቀመችበትም።

ውጤቱን ተከትሎ ማሊ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ በማድረግ በምድብ መሪነቷ ቀጥላለች።

ጋና በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም