ኢጋድ ለደቡብ ሱዳን የነጻነት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ኢጋድ ለደቡብ ሱዳን የነጻነት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የደቡብ ሱዳን 14ኛ ዓመት የነጻነት ቀን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እና መንግስት እንኳን ለነጻነት ቀናችሁ አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
ይህ ቀን በፈተናዎች ያልተበገረችው እና የኩሩዋ ሀገር የተስፋ ቃል ኪዳን የተበሰረበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ኢጋድ ለደቡብ ሱዳን ሰላም፣ አንድነት እና ልማት መረጋገጥ ቁርጠኛ እንደሆነ ገልጸው ለሰላም ስምምነቱ ሙሉ ትግበራ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የነጻነት በዓሉን በጋራ በምናከብርበት የዛሬዋ ዕለት ኢጋድ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያለውን አጋርነት ዳግም ያረጋግጣል ነው ያሉት ዋና ፀሐፊው በመልዕክታቸው።