ቼልሲ ለፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ ለፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ ክለቦች ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ ፍሉሜኔንሴን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሜትላይፍ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በ
የ60 ሚሊዮን ፓውንድ ፈራሚው ጆአኦ ፔድሮ በ18ኛው እና 56ኛው ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ ያስቆጠራቸው ግቦች ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።
ፔድሮ የልጅነት ክለቡ ላይ ግቦቹን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን በተቀዛቀዘ መልኩ ገልጿል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ እና ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል።
ቼልሲ ለግብ የቀረቡ እድሎችን በመፍጠር የተሻለ ነበር።
ጠንካራው የፍሉሜንሴ የተከላካይ መስመር በጨዋታው ላይ ባልተለመደ ሁኔታ ስህተቶችን ሲሰራ ተስተውሏል።
ቡድኑ ከ11 ጨዋታዎች በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል።
የቼልሲ የአማካይ ተጫዋች ሞሰስ ካሲዬዶ በጉዳት ምክንያት በጨዋታው ማብቂያ ላይ ወጥቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ዋንጫውን ለማንሳት ከፒኤስጂ እና ሪያል ማድሪድ አሸናፊ ጋር ያደርጋል።
ፒኤስጂ እና ሪያል ማድሪድ ነገ የሚያደርጉት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ተጠባቂ ነው።