የሶማሌ ክልል ቢሮዎች እና ዞኖች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጀመረ

ጂግጂጋ ፤ ሐምሌ 1/2017  (ኢዜአ) ፡- የሶማሌ ክልል ሴክተር ቢሮዎች እና ዞኖች የ2017 የበጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በጅግጅጋ ተጀመረ፡፡

በግምገማ መድረኩም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ ሴክተር ቢሮዎች ኃላፊዎች እና የዞን አስተዳደሮች እየተሳተፉ ነው።


 

መድረኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት  የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች፣ በምግብ ራስን የመቻል እንቅስቃሴ፣ የገቢ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣  የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የስራ አፈፃፀሞችን እንደሚገመግምም ተጠቁሟል። 

‎የግምገማ መድረኩ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም