በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማሊ ታንዛንያን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማሊ ታንዛንያን አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ማሊ ታንዛንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች ።
ማምሻውን በቤርካኔ ሙኒሲፓል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አጥቂዋ ሳራቱ ትራኦሬ በመጀመሪያ አጋማሽ ጭማሪ ደቂቃዎች ላይ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥራለች።
ማሊ በጨዋታው ብልጫ ቢወሰድባትም ያስቆጠረችውን ብቸኛ ግብ አስጠብቃ ወጥታለች።
ታንዛንያ በጨዋታው ላይ የነበራትን የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ወደ ግብ መቀየር አልቻለችም።
ውጤቱን ተከትሎ ማሊ በምድብ ሶስት በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
በዚሁ ምድብ ዛሬ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ደቡብ አፍሪካ ጋናን 2 ለ 0 አሸንፋለች። የምድቡ መሪም ሆናለች።
ጋና ከማሊ፣ ታንዛንያ ከደቡብ አፍሪካ በምድቡ የሚደረጉ ቀጣይ ጨዋታዎች ናቸው።