ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ክብር የማስጠበቅ ጉዞዋን በድል ጀምራለች - ኢዜአ አማርኛ
ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ክብር የማስጠበቅ ጉዞዋን በድል ጀምራለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት የመጀመሪያ መርሃ ግብር ደቡብ አፍሪካ ጋናን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሆነር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊንዳ ሞትልሃሎ በፍጹም ቅጣት ምት እና ጀርሜን ሲኦፖሴንዌ በጨዋታ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር የተደረገበት ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ያገኘችውን የግብ እድል በሚገባ መጠቀሟ ባለድል አድርጓታል።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ደቡብ አፍሪካ ጉዞዋን በድል ጀምራለች። ምድቧንም በሶስት ነጥብ እየመራች ነው።
ጋና ያለ ምንም ነጥብ በምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች።