አልጄሪያ ድል ቀንቷታል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29 /2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ አልጄሪያ ቦትስዋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ትናንት ማምሻውን በፔሬ ጄጎ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአማካይ ተጨዋቿ ጉቲያ ካርቹኒ በ10ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥራለች።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል ።

ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ በምድብ ሁለት በሶሰት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት በተካሄደ የመጀመሪያ ጨዋታ ናይጄሪያ ቱኒዚያ 3 ለ 0 አሸንፋለች።

ናይጄሪያ ከቦትስዋና፣ ቱኒዚያ ከአልጄሪያ በቀጣይ በምድቡ የሚደረጉ ተጫዋቾች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም