የአፍሪካ ዋንጫ ባለብዙ ክብሯ ናይጄሪያ ጉዟዋን በድል ጀምራለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ ናይጄሪያ ቱኒዚያን 3 ለ 0 አሸንፋለች።

ትናንት ማምሻውን በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም በተካሄደው አሲሳት ኦሾላ፣ ባባጂንዴ ሪንሶላ እና ቺንዌንዱ ልሄዙ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

አጥቂዋ ባባጂንዴ ሪንሶላ ግቡን ካስቆጠረች በኋላ በቅርብ በመኪና ህይወቱ ያለፈውን ዲያጎ ጆታ የደስታ አገላለጽ በመጠቀም ተጫዋቹን አስታውሳለች።

የዘጠኝ ጊዜ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫን በማንሳት የበላይ የሆነችው ናይጄሪያ ምድብ ሁለትን መምራት ጀምራለች።

ቱኒዚያ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃን ይዛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም