ሴኔጋል ድል ቀንቷታል 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29 /2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ መርሃ ግብር ሴኔጋል ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች።

በኤል ባቺር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማማ ዲዮፕ እና ንጌናር ንዳዬ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ሴኔጋል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዳለች።

ውጤቱን ተከትሎ ሴኔጋል ምድብ አንድን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት በተካሄደ የመጀመሪያ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ ከዛምቢያ ሁለት አቻ ተለያይታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም