እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ አመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል ብለዋል።

የበለጠ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው።

የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም