የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት
መንግስት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ለአብነትም ከተማ አስተዳደሩ በአመራር ዘርፍ የወጣቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ አካታች የፖለቲካ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረጉን አንስተዋል።
እንዲሁም የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማእከላት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት የከተማ አስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል።
የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በስነ-ምግባር የታነፁ በእውቀትና በአቅም የዳበሩ ወጣቶችን ማፍራት ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።
ወጣቱ የትኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር በአገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።