በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ሞርሮኮ እና ዛምቢያ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ ከዛምቢያ ሁለት አቻ ተለያይታለች።

ትናንት ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ አንድ ጨዋታ ኢብቲሳም ጂራይዲ እና ጊዝላን ቼባክ ግቦቹን ለሞሮኮ አስቆጥረዋል።

ባርባራ ባንዳ እና ራቼል ኩንዳንናንጂ ለዛምቢያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በጨዋታው ሁለቱ ሀገራት ተመጣጣኝ ፉክክር አድርገዋል።

ውጤቱን ተከትሎ በምድብ አንድ  ሞሮኮ እና ዛምቢያ በምድቡ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።

በዚሁ ምድብ ሴኔጋል ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ዛሬ ከቀኑ 11 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ከጨዋታው በፊት ደማቅ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው ውድድር 12 ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም