ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ውይይቱ በቅርብ እያደገ የመጣውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደ ነው ብለዋል።
በተለያዩ ዘርፎች የሀገራቱን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።