የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በ50ኛው የኮሞሮስ የነፃነት በዓል ለመሳተፍ ሞሮኒ፣ ኮሞሮስ ገቡ

 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2017(ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በ50ኛው የኮሞሮስ የነፃነት በዓል ለመሳተፍ ሞሮኒ፣ ኮሞሮስ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሞሮኒ ልዑል ሰይድ ኢብራሂም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

ኮሞሮስ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችው ሰኔ 29/ 1967 ዓ.ም ሲሆን በነገው ዕለት የምታከብረው 50ኛውን የነፃነት በዓሏን ነው።


 

በዘንድሮው የነፃነት በዓል ለመሳተፍ የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴን ጨምሮ የሴኔጋል፣ታንዛኒያ፣ሞሮኮ፣ማዳጋስካር፣ ሞሪታንያ እና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ኮሞሮስ መግባታቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ስፍራው ዘግቧል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም