የምስራቅ ዕዝ ለ2ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አመራሮች እያስመረቀ ነው

ባህር ዳር፤ ሰኔ 28 /2017(ኢዜአ) ፦በመከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ ለ2ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አመራሮች በብር ሽለቆ ማሰልጠኛ እያስመረቀ ነው።


 

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማ፣ ሌሎች የእዙ ከፍተኛ መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዛሬው እለት ለምርቃት የበቁት በእዝ ሰንሰለቱ መሰረት ከጓድ መሪ እስከ ክፍለጦር አመራሮች መሆናቸው ታውቋል።


 

በቆይታቸውም የወታደራዊ ስነ-ልቦና ዝግጁነት፣ የአመራር ክህሎትና እውቀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዙ ልዩ ልዩ ወታደራዊ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም