ቀጥታ፡

በዘንድሮው ዓመት 37 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦በዘንድሮው ዓመት 37 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሔደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው፡፤

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በዘንድሮው አመት ለማዕድን ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍ አስችሏል።

በ2016 በጀት ዓመት 4 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 300 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኝ ሲሆን በዘንድሮው አመት የተገኝው ገቢ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ለውጥ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፤

በዘንድሮው አመት 37 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ በማቅረብ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኝቱንም ጠቅሰዋል።

በዘርፉ  ከፍተኛ ለውጥ ለማስመዝገብ የተቻለው በኢትዮጵያ ለብዝሃ ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም