በክልሉ ለህዝቡ የልማት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት የማብቃቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል-አቶ አወሉ አብዲ

አምቦ ፤ ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ለህዝቡ  የልማት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት የማብቃቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ ገለጹ።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ በአምቦ ከተማ  ግንባታቸው የተጠናቀቁ 25 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግርም በክልሉ የህዝብን  የልማት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት የማብቃቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


 

በአምቦ ከተማ  የተገነቡት ፕሮጀክቶችም የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት የመገንባት ስራ በልዩ ትኩረት ይከናወናል ብለዋል።

የአምቦ ከተማ ከንቲባ ሃጫሉ ገመቹ፤ የከተማዋን ነዋሪዎች የረጅም ጊዜ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ለህዝብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው 25 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ተናግረዋል።


 

የፕሮጀክቶቹ ወጪም በመንግስት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎና በአጋር ድርጅቶች  የተሸፈነ መሆኑን ጠቅሰው መሰል ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላሉ ብለዋል።

በዛሬው እለት ለምርቃት ከበቁት ፕሮጀክቶች መካከል የእንስሳት ማደለቢያ፣ የወተት ላሞች እርባታ እና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ፣ ትምህርት ቤት እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡


 

የፕሮጀክቶቹ መመረቅ በአጠቃላይ ለከተማውና ለአካባቢው ነዋሪ ፋይዳቸው የላቀ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም