ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 24/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እና የከተማ አስተዳደሩና የቦሌ ክፍለ ከተማ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማን፣የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም ሚኒስትሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ልማት የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች እንደሚተከሉም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም