ፍሉሜኔንሴ ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ፍሉሜኔንሴ ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2017 (ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ማለፍ መርሃ ግብር ፍሉሜኔንሴ ኢንተር ሚላንን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በባንክ ኦፍ አሜሪካ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርጀንቲናዊው አጥቂ ጀርመን ካኖ ጨዋታው በተጀመረ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል የብራዚሉን ቡድን መሪ አድርጓል።
ብራዚላዊው የአማካይ ተጫዋች ሄርኩሊስ በ94ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል የቡድኑን አሸናፊነት አረጋግጧል።
በጨዋታው ኢንተር ሚላን በኳስ ቁጥጥር የተሻለ የነበረው ቢሆንም የፍሉሜኔንሴን አይበገሬ የተከላካይ ክፍል ሰብሮ መግባት አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ ፍሉሜኔንሴ ለሩብ ፍጻሜው ያለፈ አምስተኛ ቡድን ሆኗል።
የደቡብ አሜሪካው ክለብ የአውሮፓውን ክለብ አሸንፏል።
ፍሉሜኔንሴ በሩብ ፍጻሜው ከማንችስተር ሲቲ እና አል ሂላል አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
ማንችስተር ሲቲ ከአል ሂላል በካምፒንግ ወርልድ ስታዲየም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።