ፒኤስጂ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል - ኢዜአ አማርኛ
ፒኤስጂ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 22/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብር የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ ኢንተር ሚያሚን 4 ለ ዐ በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
ማምሻውን በሜርሴዲስ-ቤንዝ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጇኦ ኔቬስ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ አሽራፍ ሃኪሚ እና የኢንተር ሚያሚው ቶማስ አቪሌስ በራሱ ግብ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች አስቆጥረዋል።
ፒኤስጂ በጨዋታው በኢንተር ሚያሚ ላይ ፍጹም የጨዋታ የበላይነት የወሰደ ሲሆን የሚያሚ ተጫዋቾች ከራሳቸው የግብ ክልል ለመውጣትና ወደ ተጋጣሚ ቡድን መጫወቻ ስፍራ ለመድረስ እጅጉን ተቸግሮ ታይቷል።
የፓሪሱ ክለብ ጠንካራ የመከላከል አቅም፣ አስደማሚ የመሐል ሜዳ ጨዋታ እና ማራኪ የማጥቃት እንቅስቃሴን ኢንተር ሚያሚ ሊቋቋም አልቻለም።
በሊዮኔል ሜሲ እና ሉዊስ ሱዋሬዝ ልዩነት ፈጣሪነት ላይ ጥገኛ የሆነው ኢንተር ሚያሚ በጨዋታው የፒኤስጂ ፍጹም ቅጣት ክልል መድረስ ተራራን የመግፋት ያህል ከብዶት ነበር።
የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ ሶስተኛ ቡድን ሆኗል።