ባየር ሙኒክ ወደ ሩብ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 22/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ  ባየር ሙኒክ ፍላሚንጎን 4 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በሃርድ ሮክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሃሪ ኬን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሊኦን ጎሬትዝካ እና የፍላሚንጎው ኤሪክ ፑልጋር በራሱ ግብ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጌርሰን በጨዋታ እና ጆርጂኒዮ በፍጹም ቅጣት ምት ለፍላሚንጎ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ባየር ሙኒክ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል።

በሩብ ፍጻሜው ባየር ሙኒክ ከፒኤስጂ የፊታችን ቅዳሜ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ዛሬ በተደረገ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፒኤስጂ ኢንተር ሚያሚን 4 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም