ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሔዱ

አዲስ አበባ ፤ሰኔ 21/2017 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር በመሆን በጉለሌ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሒደዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም