ቀጥታ፡

የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ያስገኘ ስራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2017(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ያስገኘ ስራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ነው ብለዋል።


 

የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችያስገኘ ስራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት ከሚተከለው ችግኝ ጋር ከ47.5 ቢሊየን ገደማ እንደርሳለን ሲሉም አስታውቀዋል።

ይህም በሚቀጥለው ዓመት ከምንተክለው ጋር ሲደመር 54 ቢሊየን ልንደርስ ያስችለናል ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው።


 

በዚህ መርሃ ግብር ያመናችሁ፣ የተሳተፋችሁ እጆቻችሁ ጭቃ የነካ፥ የተከላችሁ፥ የተንከባከባችሁ ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ የምትገኙ ዲፕሎማቶች፣ ይህንን ህልም የደገፋችሁ የየትኛውም ሃገር ዜጎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፥ እንኳን ደስ ያለን ልላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

ከነገ ጀምሮ በየዕለቱ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ በሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም