በጥገና ምክንያት ዛሬ ሌሊት በተወሰኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል - ኢዜአ አማርኛ
በጥገና ምክንያት ዛሬ ሌሊት በተወሰኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ ሴንተር ወይም በሜክሲኮ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር ላይ በሚከናወን አስቸኳይ የጥገና ሥራ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢዜአ እንደገለፁት ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በሚከናወነው የጥገና ሥራ ምክንያት ከማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች ኃይል የሚቋረጥባቸው ይሆናል።
ኃይል ከሚቋረጥባቸው አካባቢዎች መካከል ሜክሲኮ፣ አፍሪካ ህብረት፣ ቄራ፣ ደንበል፣ መስቀል ፍላወር፣ ወሎ ስፈር፣ መስቀል አደባባይ፣ በባምቢስ እና አካባቢው እንደሚገኙበትም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
የጥገና ሥራው እስከሚጠናቀቅ ድረስም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።