ማንችስተር ሲቲ ጁቬንቱስን በማሸነፍ የምድቡ መሪ በመሆን አጠናቋል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የምድብ ሰባት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ጁቬንቱስን 5 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በካምፒንግ ወርልድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዠርሚ ዶኩ፣ አርሊንግ ሃላንድ፣ ፊል ፎደን፣ ሳቪኒዮ እና የጁቬንቱሱ ተከላካይ ፒዬር  ካሉሉ  በራሱ ግብ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ቲን ኮፕማይነርስ  እና ዱሳን ቭላሆቪች ለጁቬንቱስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ አስደናቂ ብቃት ያሳየ ሲሆን በተጋጣሚው ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዷል።

ሲቲ በዓለም ዋንጫው ሁሉንም የምድቡን ጨዋታዎች ያሸነፈ ብቸኛው ቡድን ሆኗል።

ማንችስተር ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ የምድቡ መሪ ሆኖ ተጠናቋል።  ጁቬንቱስ በሰባት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ሁለቱ ክለቦች ወደ ጥሎ ማለፍ መግባታቸው ይታወቃል።

በዚሁ ምድብ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ አል አይ ዋይዳድ ካዛብላካን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ካኩ በጨዋታ እና ኮጆ ላባ በፍጹም ቅጣት ምት ለአል አይን ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ካሲአስ ማይሉላ ለዋይዳድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አል አይን በሶስት ነጥብ  ሶስተኛና ዋይዳድ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም