ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ዛሬ ማምሻውን የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማን ተቀብዬ ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።