በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችን ለማስፋፋት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችን ለማስፋፋት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
ባሕርዳር፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የቱሪዝም ልማትና የመስህብ መዳረሻ ሥፍራዎችን ለማስፋፋት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በክልሉ የቱሪዝም እንቅስቃሴ፣ በቅርስ ጥበቃና ፓርኮች ልማት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የምክክር መድረክ በባህርዳር እየተካሄደ ነው።
በመድረኩም የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ክልሉ ያሉትን ዕምቅ የቱሪዝም ፀጋዎች በመጠቀም ሰፋፊ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን የማልማት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በክልሉ የሰፈነው ሰላም የቱሪዝም ፍሰቱን ለማሻሻል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።
የመድረኩ ዓላማም በክልሉ ያሉ አዳዲስ የቱሪዝም ፀጋዎችን በቀጣይ ወደ ዘርፉ ልማት ማስገባት በሚቻልባቸው ዙሪያ ላይ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
ተሳታፊዎቹ በክልሉ በቱሪዝም ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ አዳዲስ መዳረሻ ቦታዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱም ታውቋል።