ኢንተር ሚላን እና ሞንቴሬይ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብተዋል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የምድብ አምስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተደርገዋል።

በሉመን ፊልድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢንተር ሚላን ሪቨር ፕሌትን 2 ለ ዐ አሸንፏል።

ፍራንቼስኮ ፒዮ ኤስፖሲቶ እና አሌሳንድሮ ባስቶኒ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሉካስ ማርቲኔዝ ኳርታ እና ጎንዛሎ ሞንቲዬል ከሪቨር ፕሌት በኩል በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢንተር ሚላን በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ በመሆን ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።

ሪቨር ፕሌት በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

በዚሁ ምድብ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ሞንቴሬይ ኡርዋ ሬድ ዳይመንድስን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

ጀርመን ቤትራሜ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጄሱስ ኮሮና እና ኔልሰን ዲኦሳ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ሞንቴሬይ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብቷል።

በምድቡ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኡርዋ ሬድ ዳይመንድስ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከሞንቴሬይ፣ ኢንተር ሚላን ከፍሉሜኔንሴ በጥሎ ማለፉ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም