ቀጥታ፡

መቀሌ 70 እንደርታ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወረደ 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አጥቂው እዮብ ገብረማርያም ጨዋታው በተጀመረ በአራተኛ ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ በ41 ነጥብ 15ኛ ደረጃን በመያዝ ከሊጉ የወረደ አራተኛ ክለብ ሆኗል። በሊጉም 13ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል። 

ድል የቀናው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ44 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 12ኛ ከፍ በማድረግ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል። በውድድር ዓመቱም 11ኛ ድሉን ተቀዳጅቷል። 

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ስሑል ሽሬ እና አዳማ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረዱ ክለቦች ናቸው።

ነገሌ አርሲ እና ሸገር ከተማ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸው ይታወቃል።

ቀን ላይ በተደረገ የ36ኛ ሳምንት ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም