ቀጥታ፡

ቤኔፊካ ወደ ጥሎ ማለፍ ገብቷል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 17/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ በምድብ ሶስት ቤኔፊካ ባየር ሙኒክን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በባንክ ኦፍ አሜሪካ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንድሪያስ ሼልድሩፕ በ13ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል።

ባየር ሙኒክ በሁለተኛው አጋማሽ ግልፅ የግብ እድሎችን ቢፈጥርም ሊጠቀምበት አልቻለም።

ውጤቱን ተከትሎ ቤኔፊካ በምድብ ሶስት በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ ሆኖ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።

ወደ ጥሎ ማለፉ አስቀድሞ መግባቱን ያረጋገጠው ባየር ሙኒክ በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

የጀርመኑ ክለብ በውድድሩ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ቤኔፊካ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ባየርሙኒክን አሸንፏል።

በዚሁ ምድብ በጂኦዲስ ፓርክ ስታዲየም  የተደረገው የቦካ ጁኒየርስ እና ኦክላንድ ሲቲ ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የኦክላንድ ሲቲ ግብ ጠባቂ ናታን ጋሮው በ26ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ ያስቆጠራት ጎል ቦካ ጁኒየርስን መሪ አድርጎ ነበር።

ክርስቲያን ግሬይ በ52ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ኦክላንድ ሲቲ አቻ ሆኗል። ቡድኑ በውድድሩ ላይ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።

ጨዋታው 55ኛው ደቂቃ ላይ በመጥፎ አየር ንብረት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ነበር።

ቦካ ጁኒየርስ በሁለት ነጥብ ሶስተኛ፣ ኦክላንድ ሲቲ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም