ፍሉሜንኔሴ በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ):- በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ በምድብ ስድስት መርሃ ግብር ፍሉሜኔንሴ ኡልሳንን 4 ለ 2 አሸንፏል።

ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ በኒው ጀርዚ ሜት ላይፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጆን አሪያስ፣ ኖናቶ፣ ሁዋን ፍሬይቴስ እና ኬኖ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጂን ዩን-ሊ እና ዎን-ሳንግ ኡም ለኡልሳን ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ በፊፋ የክለቦቾ ዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው ፍሉሜኔንሴ በአራት ነጥብ ምድብ ስድስትን መምራት ጀምሯል።

ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የኮሪያ ሪፐብሊኩ ክለብ ኡልሳን ከውድድሩ ተሰናብቷል።

በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ማሜሎዲ ሳንዳውንስን 4 ለ 3 አሸንፏል።

በተመሳሳይ ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ በምድብ አምስት በተካሄደ ጨዋታ ሪቨር ፕሌት እና ሞንኔቴሬይ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በካሊፎርኒያ ሮዝ ቦውል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሪቨር ፕሌት የአማካይ ተጫዋች ኬቨን ካስታኖ በ91ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሪቨር ፕሌት ምድብ አምስትን በአራት ነጥብ እየመራ ነው።

በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ኡርዋ ሬድ ዳይመንድስን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም