የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፤ሰኔ 14/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ንጉሥ ታደሰ (ዶ/ር)፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተማሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪና በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።
ከተመራቂዎች መካከል 1 ሺህ 774 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 538ቱ ደግም ሴቶች ናቸው።