ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ አልቤርቶ ቫርኔሮ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የግንባታ ከባቢ እና ታሪካዊነት ያላቸው ምልክቶችን ላቅ ባለ ደረጃ የቀረፀ ነው ብለዋል።

ከታሪካዊ ስራዎቻቸው መካከል የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል፣ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ፣ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሥራ ይገኙበታል።

የሥራ ውርሳቸው በነዚህ ብሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ እንደሚኖር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ለነፍሳቸው ረፍትን፣በረፍታቸው ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም