ቀጥታ፡

ፓልሜራስ አል አህሊን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ):- በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ በምድብ ሁለት በተደረገ ጨዋታ የብራዚሉ ፓልሜራስ የግብጹን አል አህሊን 2 ለ 0 አሸንፏል። 

ማምሻውን በኒው ጀርዚ  ሜትላይፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሆዜ ማኑኤል ሎፔዝ እና የአል አህሊው ዌሳም አቡ አሊ በራሱ ግብ ላይ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ጨዋታው መብረቅ እና ከፍተኛ ዝናብ በቀላቀለ ኃይለኛ የአየር ንብረት ምክንያት ለ50 ደቂቃ ተቋርጦ ነበር።  

ውጤቱን ተከትሎ ፓልሜራስ ምድብ አንድን በአራት ነጥብ ምድቡን መምራት ጀምሯል። 

በሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ያገኘው አል አህሊ ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ያለውን ተስፋ ለማለምለም በምድብ የመጨረሻ ጨዋታው ፖርቱን የማሸነፍ ግዴታ ውሰጥ ገብቷል። 

በዚሁ ምድብ በአሁኑ ሰዓት ኢንተር ሚያሚ እና ፖርቶ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም