ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 11/2017(ኢዜአ):- በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ በምድብ ሰባት በተደረገ የመጀመሪያ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ዋይዳድ ካዛብላንካን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በፊላደልፊያ ሊንከን ፋይናንሻል ፋልድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፊል ፎደን እና ዠረሚ ዶኩ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የማንችስተር ሲቲው የቀኝ ተመላላሽ ሪኮ ሉዊስ በ88ኛ ደቂቃ በሳሙኤል ኦቤንግ ላይ በሰራው ጥፋት በአወዛጋቢ ሁኔታ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) የብራዚላዊውን ዋና ዳኛ ራሞን አባቲን ውሳኔ አጽንቷል።
ሉዊስ አስቀድሞ ኳሱን ካገኘ በኋላ የሰራው ጥፋት ከቢጫ ካርድ ያለፈ ቅጣት ሊያሰጠው አይገባም የሚሉ አስተያየቶች በመሰንዘር ላይ ናቸው።
ፊል ፎደን የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል። ራሱ ግብ ከማስቆጠር ባለፈ ለዶኩ ጎል መቆጠር አስተዋጽኦ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ምድብ ሰባትን በሶስት ነጥብ ምድቡን መምራት ጀምሯል።
በዚሁ ምድብ አል አይን እና ጁቬንቱስ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።