የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሃ ግብር ማሻሻያ ተደረገበት - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሃ ግብር ማሻሻያ ተደረገበት
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የሰዓት ለውጥ ማድረጉን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።
ማሻሻያው የመጨረሻውን የመዝጊያ ጨዋታ በተለየ ሁኔታ ማከናወን፣ የቀጥታ ስርጭት ተደራሽነትን ፣ የክለቦችን ውጤት እና የመጫወቻ ሜዳዎች ያሉበትን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አመልክቷል።
በዚህም መሰረት 36ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከእሁድ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐሙስ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ታውቋል።