የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ የውድድር ዓመት ነሐሴ 9 ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ የውድድር ዓመት ነሐሴ 9 ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2017 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 2025/26 መርሃ ግብር ዛሬ ይፋ ሆኗል።
በሊጉ የመክፈቻ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቦርንማውዝ የሚያደርገው ጨዋታ የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ መርሃ ግብር ነው።
ዎልቭስ ከማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ፣ ሰንደርላንድ ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከበርንሌይ፣ አስቶንቪላ ከኒውካስትል ዩናይትድ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከብሬንትፎርድ፣ ሊድስ ዩናይትድ ከኤቨርተን እና ብራይተን ከፉልሃም ሌሎች የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ናቸው።
በውድድር ዓመቱ 380 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ፕሪሚየር ሊጉ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።