ሪቨር ፕሌት በመጀመሪያ ጨዋታው ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ሪቨር ፕሌት በመጀመሪያ ጨዋታው ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 11/2017(ኢዜአ):- በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ በምድብ 5 በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ሪቨር ፕሌት ኡርዋ ሬድ ዳይመንድስን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በሉመን ፋልድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፋኩንዶ ኮሊዲዮ፣ ሰባስቲያን ድሩሲ እና ማክሲሚሊያኖ ፔዛ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ዩሱኬ ማቱሱዎ በፍጹም ቅጣት ምት ለኡርዋ ሬድ ዳይመንድስ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የሪቨር ፕሌቱ አርጀንቲናዊ የግራ መስመር ተጫዋች ማርኮስ አኩና የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። አኩና ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።