ቼልሲ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ሰኔ 10/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ ክለቦች ዓለም ዋንጫ ቼልሲ ሎስ አንጀለስ ኤፍሲን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሜርሴዲስ- ቤንዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፔድሮ ኔቶ በ34ኛው እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ79ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ቼልሲ ከተጋጣሚው በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል በመፍጠር የተሻለ ነበር። 

ፔድሮ ኔቶ የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል። 

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ ምድብ ሶስትን በሶስት ነጥብ  መምራት ጀምሯል።

በዚሁ ምድብ ፍላሚንጐ ከኤስፔራንስ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በሊንከን ፋይናንሺያል ፊልድ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በምድብ 3 ቦካ ጁኒየርስ ከቤኔፊካ ከሌሊቱ  7 ሰዓት ላይ በሀርድ ሮክ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም