የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖን ለመከላከል አካታች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አማራጮችን ማፈላለግ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖን ለመከላከል አካታች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አማራጮችን ማፈላለግ ይገባል
አዲስ አበባ፤ሰኔ 9/2017(ኢዜአ)፦በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖን ለመከላከል አካታች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አማራጮችን ማፈላለግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ኢትዮጵያ ከጷጉሜ 3 እስከ 5 የምታስተናግደውን ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባዔ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ህብረት የግብርናና ገጠር ልማት፣ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ናቸው።
በዚሁ ወቅት አፍሪካ ለዓለም አየር ንብረት ለውጥ ዝቅተኛ ድርሻ ቢኖራትም የችግሩ ዋነኛ ገፈት ቀማሽ መሆኗ ተነስቷል።
ይህን ችግር በዘላቂነት ለመከላከል የአገራት ትብብር ሊጠናከር እንሚገባና የበለፀጉ አገራትም ለአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል ቃል የገቡትን የፋይናንስ ድጋፍ ሊተገብሩ እንደሚገባም ተመልክቷል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው።
ከዚህም ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመው፥ኢትዮጵያ እኤአ ከ2019-2023 አርባ ቢሊዮን ችግኞችን መትከሏንም አንስተዋል።
የታዳሽ ሃይልን ከማስፋትና የአረንጓዴ ከተሞች ግንባታ ላይም ሰፊ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።
የአፍሪካ ህብረት አባል አገራትና አጋር ድርጅቶች ለአህጉሪቱ አየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት አጀንዳን እንዲያራምዱ አዳዲስ የፋይናንስና ኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት ይገባል ብለዋል።
ጉባኤው የፋይናንስ አቅምን ለማጠናከር ሁለንተናዊ ቅንጅቶችን ለማጎልበት ወሳኝ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተውታል።
የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ለመደገፍ መንግስታት አጋር ድርጅቶች የምርምር ተቋማትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት እንዲደግፉም ጠይቀዋል።
በአፍሪካ ህብረት የግብርናና ገጠር ልማት፣ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በበኩላቸው፤ አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላት አስተዋፅኦ ከአራት በመቶ የሚበልጥ ባይሆንም የቀውሱ ዋነኛ ሰለባ ሆናለች ብለዋል።
ይህም በዜጎች ጤናና በከባቢ ላይ ከባድ ጉዳትን እያስከተለ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የንጹህ ውሃና የምግብ ዋስትና ላይም ተጽዕኖው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።
አፍሪካ ከዚህ ቀውስ መውጣት እንድትችል የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን በማንሳት።