ቀጥታ፡

ምሁራን አጀንዳዎቻቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል - ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2017(ኢዜአ)፦ ምሁራን አሉን የሚሏቸውን አጀንዳዎች በቀጥታ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በምክክር ሂደቱ ዙሪያ ግብዓት ለማሰባሰብና ይበልጥ ተቀራርቦ መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከምሁራን ጋር እየተወያየ ነው።


 

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና ምሁራን ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እንዳሉት፤ ሀገር ለሀሳብ ልዩነቶችና አለመግባባቶች መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ብሎም በመመካከር ሁሉን አሸናፊ የሚያደርግ ውጤት ላይ መድረስ የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናት።

ለዚህም የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች እንደምትገኝ አስረድተው ምሁራንም በምክክሩ ሂደት በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ምክክሩ እንደሀገር የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስገኝ የምሁራን ሚና ጉልህ መሆኑም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ምሁራን በምክክር ሂደቱ እንዲካተቱና ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

በዚህም ምሁራን በአጀንዳ ልየታ ሕዝባዊ መድረኮች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ከማመቻት ባለፈ አሉን የሚሏቸውን አጀንዳዎች በቀጥታ ለኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰዋል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም