ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን 3 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዲስ ግደይ፣ ኪቲካ ጅማ እና ዩጋንዳዊው ሳይመን  ፒተር የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ካርሎስ ዳምጠው እና እዮብ ተስፋዬ ለወላይታ ድቻ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። ከወራጅ ቀጠና ስጋት በመጠኑም ቢሆን የራቀበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

ወላይታ ድቻ በ45 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ይዟል።

ቀን ላይ በተደረጉ  ጨዋታዎች መቀሌ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መቻልን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

አዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

በቀጣዩ ሳምንት በሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማን ይወርዳል? እና ማን ይተርፋል? የሚለው ጉዳይ አጓጊ ሆኗል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ስሑል ሽሬ አስቀድመው ከሊጉ የወረዱ ክለቦች ናቸው።

ቀሪ ሁለት ወራጅ ክለቦች በ36ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይታወቃሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም