ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን - ኢዜአ አማርኛ
ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
አዲስ አበባ፤ሰኔ 8/2017(ኢዜአ)፦ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
የህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን " ህዳሴን በህዳሴ ኮር " በሚል መሪ ሐሳብ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አክብሯል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአብሮነትና የብልጽግና ተምሣሌት ማሣያ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትም የህዳሴ ግድቡ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
ሠራዊቱ ለህዳሴ ግድቡ ደህንነት መጠበቅና የአካባቢው ሰላም እንዲረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የመከላከያ ሠራዊት የሀገር መከታ መሆኑን ጠቁመው፥ ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን እና የህዝብ አለኝታነቱን በተግባር እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስትም ሠራዊቱ ተልዕኮውን በሚገባ እንዲወጣ የሚያደርገውን ዘርፍ ብዙ አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ፣የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፣ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሠለ መሠረት፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ታድመዋል።