በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ ኢንተር ሚያሚ እና አል አህሊ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ ኢንተር ሚያሚ እና አል አህሊ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ ሰኔ 8/2015(ኢዜአ):- በመጀመሪያው የፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ በምድብ 1 በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ኢንተር ሚያሚ እና አል አህሊ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በሀርድ ሮክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አል አህሊ በ42ኛው ደቂቃ ያገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት አጥቂው መሐሙድ አህመድ ኢብራሂም ሀሰን (ትርዝጌት) ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
የኢንተር ሚያሚው ግብ ጠባቂ ኦስካር አልፍሬዶ ኡስታሪ ፍጹም ቅጣት ምቱን አድኗል። አርጀንቲናዊው የግብ ዘብ የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
ከጨዋታው በፊት በሚያሚ በሀርድ ሮክ ስታዲየም የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሄዷል።
የፊፋ የክለቦች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ውድድር ሲሆን 32 ቡድኖች በስምንት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።